Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dpw

Department of Public Works
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Amharic (አማርኛ)

This page contains information about The Department of Public Works services for Amharic speakers.

የDPW አጠቃላይ መረጃ         

  
የኤጀንሲው ስም:   የዲ.ሲ. የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ
ተልዕኮ: 
የዲ.ሲ. የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW)  ተልዕኮ ተመጣጣኝ እና የተሟላ አካባቢ ያለው የህዝብ አገልግሎቶችን መስጠት ነው። 
ዋና ፕሮግራሞች/የክፍሉ ገለፃ፡
የደረቅ ቆሻሻ አወገዳድ አስተዳደር
የዲ.ሲ. የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ አስተዳደር ቆሻሻ እና ሪሳይክል የሚደረጉ ስብስቦችን፣ የንጽህና አጠባበቅ ትምህርትና አፈጻጸሞች፣ ያረጁ ምልክቶችን ማስወገድ፣ የህዝብ ቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች፣ የረገፉ ቅጠላ ቅጠሎችን መሰብሰብ እና የውስጥ መንገድና አስፋልት ጠረጋዎችን የሚያካትቱ ስራዎችን በየቀኑ ያከናውናል።    

የመኪና ማቆሚያ ደንብ አስከባሪ አስተዳደር 
የዲሲ የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) የመኪና ማቆሚያ ደንብ አስከባሪ አስተዳደር ጉዳት የሚያደርሱና የተጣሉ ተሽከርካሪዎችን ማስወገድ እና መቅጣት፣ መጎተት፣ የማቆሚያ ህግን በመተላለፍ የቆሙ ተሽከርካሪዎችን ወደ ተዘጋጀ ቦታ በመውሰድ የመቆለፍና የማቆም ተግባራትን ያከናውናል።

የተሽከርካሪዎች አያያዝ አስተዳደር
የዲሲ የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) የተሽከርካሪዎች አያያዝ አስተዳደር ተሽከርካሪዎችን በማቅረብ፣ ነዳጅ በመሙላትና በሺ የሚቆጠሩ የዲስትሪክቱን ከአነስተኛ እስከ ከባድ ተሽከርካሪዎችን በመጠገን የከተማ ውስጥ ሥራዎችን ይደግፋል። የተሽከርካሪዎች አስተዳደር ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑና ተለዋጭ-ነዳጅ ተጠቃሚ (ምሳሌ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ) የሆኑ ተሽከርካሪዎችን በመግዛት ለከተማው ያቀርባል።

አገልግሎቶች:
የጠባብ መንገዶች ጽዳት  
የዲሲ የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) የህዝብ ጠባብ መንገዶች ንጹህ እንዲሆኑና ሠራተኞች ከፀደይ እስከ በልግ ባለው ጊዜ በከተማው አካባቢ በቀላሉ እንዲዘዋወሩ ለማረጋገጥ ጠንክሮ ይሰራል። 
የመኪና ሀራጅ  
የዲ.ሲ. መንግሥት ትርፍ ንብረቶቹን በኦንላይን በሀራጅ ይሸጣል። በበለጠ ለመረዳት “www.dcgovt.govdeals.com” ን ይመልከቱ።  
መቆለፍና ማሰር  
የዲስትሪክቱ ሀግ 60 ቀናት  የሆነው ሁለት ወይም ከዛ በላይ የሆነ ያልተከፈለ የፓርኪንግ እና/ወይም የፎቶ  ትኬት ያለው ተሽከርካሪ እንዲታሰር ይደርጋል።  የዲሲ የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) ሠራተኞች ህግ የተላለፉ ተሽከርካሪዎች ታርጋን መለየት በሚችል ቴክኖሎጅ (LPRS) ተጠቅመው ይፈልጋሉ።
የተጠራቀመ ቆሻሻ መሰብሰብ 
የዲሲ የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW)  የቆሻሻ መሰበሰብ አገልግሎት ለሚያገኙ የመኖሪያ ቤቶች ግዙፍ የሆኑ ዕቃዎችን በቀጠሮ ይሰበስባል።  ይህም የአንድ ቤተሰብ መኖርያ ቤቶችን እና ሦስት ወይም ከዛ በታች የመኖሪያ ዩኒቶች ያላቸውን የመኖርያ ህንፃዎችን ያካትታል።  
የሞቱ እንስሳዎችን  መሰብሰብ 
የዲሲ የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) የሞቱ እንስሣዎችን ክሕዝብ ቦታዎች ብቻ ይሰበስባል። ቁሻሻ እንዲነሳልዎት ከፈለጉ 311 ይደውሉ።   
የቆሻሻ እና ሪሳይክል የሚደረጉ ዕቃዎች የሚሰበሰቡበትን የጊዜ ሰሌዳ ያግኙ  
አብዛኛዎቹ ቤተሰቦች በሳምንት አንድ ጊዜ የቆሻሻ አሰባሰብ የጊዜ ሰሌዳን ይከተላሉ።  የእርስዎን የቆሻሻ መሰብሰቢያ ቀን (ናት) ለማወቅ ቆሻሻ እና ሪሳይክል የሚደረጉ ዕቃዎች የሚሰበሰቡበትን ቀን (ቀናት) ለማወቅ የስማርት ስልክ “አፕን”


የፎርት ቶተን የማዘዋወሪያ ጣቢያ  
የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ የአካባቢው ነዋሪዎች ደረቅ ቆሻሻን፣ የቤተሰብ አደገኛ ቆሻሻዎችን እና አስፈላጊ ያልሆኑ የኤሌክትሪክ መሣሪያዎችን እንዲያስወግዱና የማይፈለጉ የግል ማስረጃዎችን ቀዳደው መጣል እንዲችሉ የፎርት ቶተን የማዘዋወሪያ ጣቢያን አዘጋጅቷል።
በአካባቢ ላይ የሚታዩ ምልክቶችን ማስወገድ
በየቦታው የሚታዩ ምልክቶች በዲሲ ውስጥ ዋና ችግሮች ሲሆኑ ዲስትሪክቱ ንጹህና ጤናማ  የሆነ አካባቢን ለኗሪዎችና ለጎብኝዎች በማቅረብ ረገድ ችለተኛ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።   
የአካባቢ ጽዳት ድጋፍ 
የዲሲ የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) የቅዳሜ የአካባቢ ጽዳት ፕሮጀክትን የሚያቀናጁ የማህበረሰብ ቡድኖችን በአካባቢ ጽዳት ፕሮጀክቶች አማካኝነት ይረዳል። ፕሮግራሙ የሥራ መሣሪያዎችን ማለትም ሀያ የቆሻሻ መጣያ የፕላስቲክ ከረጢቶችን፣ መጥረጊያ ብሩሾችንና ወደ ሰባት የሚሆኑ የቆሻሻ (ቅጠል፣ በረዶ የመሳሰሉትን) መሰብሰቢያ መሣሪያዎችን ያውሳል።   
የዓመት በዓል ቆሻሻና ሪሳይክል የሚደረጉ እቃዎች መሰብሰቢያ የጊዜ ሰሌዳ      Holiday Trash and Recycling Collection Schedule
በዓላት ቆሻሻ ወይም ሪሳይክል የሚደረጉ ዕቃዎች የሚሰበሰቡባቸውን ቀን ሊቀይሩ ይችላሉ። የመሰብሰቢያ ጊዜያትን ለማወቅ ይህንን መረጃ ይመለከቱ። 
አደጋኛ የሆኑ የቤት ቅሻሻዎችና ሰነዶችን ቀዶ መጣያዎች እና ”ኢ-ሳይክሊንግ”
በፎርታተን የማዘዋወሪያ ጣቢያ ላይ አደገኛ የሆኑ የቤት ቆሻሻና የማይፈለጉ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎችና የግል ሰነዶች በመጠቀም ከዓመት በዓል ቀናቶች በስተቀር ወር በገባ የመጀመሪያ ቅዳሜ ከ8 am እስከ 3 ፒኤ pm ባለው ጊዜ ማከናወን ይቻላል።  
ቅጠልና የዓመት በዓል ዛፍ አሰባሰብ
የጸደይ ቅጠል አሰባሰብ ፕሮግራም ከህዳር የመጀመሪያው ሳምንት እስከ ጥር የመጀመሪያው ሳምንት ድረስ ባለው ወቅት ይከናወናል። 
ቆሻሻና በአካባቢ ላይ የሚታዩ ምልክቶችን መከላከል   
ቆሻሻና በአካባቢ ላይ የሚታዩ ምልክቶች ወይም ቅቦች የህዝብ እክሎች ሲሆኑ ለማሰውገድም ነዋሪዎችንና ዲስትሪክቱን ከገንዘብ ያለፈ ወጪ ያስወጡታል።   
የቆሻሻ መጣያ ገንዳ አሰባሰብ እና አረማመጥ
የቆሻሻ መጣያ ገንዳ እነደ አካባቢው ሁኔታ ሲለያይ በሳምንት ከአንድ ቀን እስከ ሦስት ቀናት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በምሽት ቆሻሻው ይወሰዳል።  የቆሻሻው ገንዳዎች ከመኖሪያ አካባቢዎች እንዲርቁ የሚደረገው ቆሻሻው ሲሰበሰብ ድምጽ ስለሚኖረው ነው። 
የተጎተተ ማኪናን ማግኘት   
መኪናዎ ተጎትቷል ብለው ካመኑ የመጎተቻ ቁጥጥር ማዕከልን በ(202) 541-6083 ይደውሉ።፡፡ 
የመኪና ማቆምያ ትኬት በኦንላይን መክፈል  
የዲ.ሲ. የሞተር ተሽከርካሪዎች ክፍል ትኬት በኦንላይን እንዲከፍሉ ይፈቅዳል። 
ሪሳይክል የሚደረጉ እቃዎች አሰባብሰ
የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች ሪሳይክል የሚደረጉትን ከአንድ ቤተሰብ መኖሪያ ቤቶችና ሦስት ወይም ከዛ በታች ነዋሪ ያላቸው አፓርትመንቶች   በሳምንት አንድ ጊዜ ይሰበስባል።  የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) ለተለያየ አገልግሎት ማለትም ለንግድና ለመኖርያ ከሚያገለግሉ ህንጻዎች ወይም አራት እና ከዛ በላይ ነዋሪ ከሚኖርባቸው የመኖሪያ ህንጻዎች  ቆሻሻ አይሰበስብም።  
የሪሳይክል ማጠራቀሚያ ገንዳ ጥገና እና ግዥ
የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ ቢጠፋብዎ ወይም ጥገና ቢያስፈልገው ምን ያደርጋሉ? አዲሲ ገንዳ እንዴት መጠየቅ እንደሚችሉ ወይም የተበላሸውን ማስተካከል እንዲሚችሉ ይወቁ።
አደገኛና የተጣሉ ተሽከርካሪዎችን እንዴት ማስወገድ እንደሚችሉ
የዲሲ የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) መርማሪዎች የተጣሉና አደገኛ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ለመርመርና ከህዝብና ክግል ንብረቶች ለማስወገድ በዲስትሪክቱ ውስጥ ይዘዋወራሉ።  አደገኛ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ቲኬት ከተሰጣቸው በኋላ ከህዝብና ከግል ንብረቶች ወዲያውኑ እንዲወገዱ ሊደረጉ ይችላሉ።  
የተሽከርካሪ ማቆሚያ ደንብ የማስከብር ጥያቄ
የዲሲ የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) የመኪና ማቆሚያ ደንብ አስከባሪ አስተዳደር ጉዳት የሚያደርሱና የተጣሉ ተሽከርካሪዎችን ማስወገድ፣ መቅጣት፣ መጎተት፣ የማቆሚያ ህግን በመተላለፍ የቆሙ ተሽከርካሪዎችን ወደ ተዘጋጀ ቦታ በመውሰድ የማሰርና የማቆም ተግባራትን ያከናውናል።
የመኖሪያ እና የንግድ መንገድ የጠረጋ ጊዜ ሰሌዳ
የዲሲ የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) የተለያዩ ቅርጾች ያላቸውን መጥረጊያዊች በመጠቀም በመኖሪያ አካባቢ የሚገኙ የውስጥ መንገዶችን ያጸዳል. በየዓመቱ በመጋቢትና ጥቅምት መካከል እነዚህ የጽዳት ሠራተኞች  በመኖሪያ ቤት አካባቢና በጽዳት ሰዓት ማቆም ክልክል መሆኑን የሚገልጹ የማቆሚያ ሰዓት ገደብ ምልክት ባለባቸው መንገዶች ይሠራሉ።


 

የቅጣት (ቲኬት) ምስልን በ”TICPIX” መፈለግ 
የመኪና ማቆሚያ ህግን የመተላለፍ ቅጣት ቲኬት ከደረስዎትና የተላለፉትን ህግ የሚያሳይ ምስል ለማየት ከፈለጉ የ”TicPix app” ተጠቅመው ማየት ይችላሉ።
በረዶ ማስወገድ
የዲስትሪክቱ የበረዶ ቡድን ከሌሎች የዲ.ሲ. መንግሥት አካላት ጋር በመተባበር የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች ክፍለን እና የዲስትሪክቱን የትራንስፖርት ዲፓርትመንትን በማካተት የተዋቀረ ነው። የበረዶ ቡድኑ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴን ደህንነት ለመጠበቅ በየመንገዶቹ የሚገኝ በረዶን ያጸዳል።  
የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ትምህርትና ደንብ ማስከበር (SWEEP) ፕሮግራም የዲስትሪክቱን ንጽህና ለመጠበቅ መርማሪዎችንና ተቆጣጣሪዎችን ከነዋሪዎችና የንግድ ድርጅቶች ጋር እንዲሠሩ ይረዳቸዋል። 
የቲኬት ቅጣት
የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) የዲስትሪክቱን የማቆሚያ ደንቦች ለሚተላለፉ ተሽከርካሪዎች የማቆሚያ ቅጣት ቲኬትን ይሰጣል። በብዛት ከሚከሰቱት ጥሰቶች ውስጥ  የሚከተሉትን ያካትታል፤- ጊዜው ያለቀበት ሚተር ላይ ማቆም፣ በመኖሪያ አካባቢ ከሚፈቀደው ጊዜ በላይ ማቆም፣ በጠዋትና ከሰዓት በኋላ ባሉ የአጣዳፊ ትራፊክ ሰዓቶች በተከለከሉ ቦታዎች ማቆም እና ጊዜው ያለፈባቸው ታርጋዎች። 
መጎተት
የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) የመጎተቻ አሽከርካሪዎች ተሽከርካሪው በማንኛውም የማቆሚያ ደንብ መተላለፍ ምክንያት ቲኬት ከተሰጠው በኋላ ሊጎትቱ ይችላሉ።  በህጋዊ መንገድ የቆሙ ተሽከርካሪዎችም ቢሆኑ በድንገተኛ ምክንያቶች ለምሳሌ ፕሬዚደንቱ በከተማው ውስጥ በሚዘዋወርበት ጊዜ በሜትሮፖሊታን የፖሊስ ዲፓርትመንት የደህንነተ አገልግሎት በሚቀርብ ጥያቄ ሊጎተቱ ይችላሉ። 
ቆሻሻ አሰባሰብ
የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) ቆሻሻን በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ከአንድ ቤተሰብ የመኖሪያ ቤቶችና ሶስት እና ከዛ በታች ነዋሪ የሚንኖርባቸው የመኖሪያ ህንጻዎች ይሰበስባል። የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) በተጨማሪም ግዙፍ የሆኑ ዕቃዎችን የ”DPW” የቆሻሻ መሰብሰቢያ አገልግሎት ካላቸው መኖሪያ ቤቶች በቀጠሮ ይሰበስባል።  
የባዶ መሬት ጽዳት - ሳር እና አረም ማጨድ           
ዉሀ ያለባቸው ባዶ የመሬት ቦታዎች ቆሻሻ መድፋትን ስለሚያበረታቱ በብዛት አይጥና የወባ ትንኞችን ይስባሉ።  በነዚህ ቦታዎች ላይ የሚጫወቱ ልጆችም ጉዳት ሊያጋጥማቸው ይችላል። የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) እነዚህን ንብረቶች ከቆሻሻና ከአረም ነጻ ለማድረግ ከሌሎች የመንግሥት አካላት ጋር በአንድነት ይሠራል።  
የግቢ ቆሻሻ መሰብሰብ  
የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) የቆሻሻና ሪሳይክል የሚደረጉ ዕቃዎች  መሰብሰቢያ አገልግሎት ተጠቃሚ ለሆኑ የመኖሪያ ቤቶች በሳምንት እስከ አምስት ከረጢቶች የግቢ ቆሻሻ ይሰበስባል።  የህዝብ አገልግሎት ሥራዎች መምሪያ (DPW) ቅድሚያ የሚሰጠው ለቆሻሻ ሲሆን በግቢ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ቆሻሻዎች ግን በትራኩ ውስጥ በቂ ቦታ ካለ ብቻ ይሰበሰባሉ።                                 

የትርጉም አገልግሎቶች: 
የህዝብ አገልግሎት ሥራዎችን በሚመለከት በሌላ ቋንቋ ማነገጋገር ከፈለጉ እባክዎን በ(202) 673-6833 ይደውሉ። አንዱ ሠራተኛችን በቀጥታ ሊረዳዎት ከሚችል አስተርጓሚ ጋር ያገናኝዎታል።   

አድራሻችን:
DC Department of Public Works
2000 14th Street, NW
6th Floor
Washington, DC 20009
202-673-6833
www.dpw.dc.gov